የኢትዮጵያና ኤርትራ የዛላምበሳ ድንበር ተዘጋ

ፎቶ ፋይል

የኢትዮጵያና የኤርትራ የዛላንበሳ ድንበር ዛሬ መዘጋቱን የትግራይ ክልል የጉሎ መኸዳ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ የዛላንበሳ ድንበር ዛሬ መዘጋቱን የትግራይ ክልል የጉሎ መኸዳ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

ድንበሩ የሁለቱም ሃገሮች መሪዎች በአካል በተገኙበት የተከፈተው በያዝነው የኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ነበር።

የሁለቱም ሃገሮች የሆኑ ሰዎች ከሦስት ወራት በላይ ሲመላለሱበት የቆየው ድንበር የተዘጋው ከኤርትራ በኩል መሆኑን የወረዳው የፀጥታው ኃላፊ አቶ ግርማይ ሃዱሽ አመልክተዋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረ ድረስ ስለንድበሩ መዘጋት የኤርትራ መንግሥት የሰጠው መግለጫ ወይም በይፋ ያሳወቀው ምክንያት የለም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያና ኤርትራ የዛላምበሳ ድንበር ተዘጋ