ባሳለፍነው ሳምንት በቤንሻንጉል ክልል በተፈጠረ ግጭት የስምንት ሰው ሕይወት ማለፉ ተነግሯል። በነቀምቴም እንዲሁ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሼ ዞን በሎጂጋንፎይ ወረዳ በሁለት ግለሰቦች ምክኒያት በተነሳ ግጭት የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልልሉ መንግስት አስታወቀ። ግጭቱ ከብሔር ግጭት ጋር የሚገናኝ ነገር የለውም ብሏል።
በሌላ ዜናም በነቀምቴ ከተማ በተነሳ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል። የአረና ትግራይ ቃል አቀባይ ጥቃቱ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ነው ብለውታል።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
Your browser doesn’t support HTML5
በቤንሻንጉል ስምንት በነቀምቴ ሦስት ሰዎች ተገደሉ