ከሃገር ውጭ የሚገኙ ሁለት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር የተካሄደ ውይይት ነው።
“የመጭው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ማንነት በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ዓይን እንዴት ታየ? ለውጡንስ እንደምን ተቀበሉት?” በሚሉ ጭብጦች የሚንደረደረው ውይይት፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር በአገሪቱ የሚታዩትን አሳሳቢ ሁኔታዎች ለመፍታት ሊከተሉ የሚችሉሏቸውን አቅጣጫ፤ ዕድል እና ፈተናዎቻቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ድርሻ ጨምሮ በሁለቱ ተወያዮች ዕይታ ለመዳሰስ ይጥራል።
ዶ/ር አብይ አሕመድ በጠቅላይ ሚንስትርነት የሚመሯት አገር ምን መልክ ይኖራት ትሆን? ውይይቶቹን ያድምጡ እና የቀጣዩ ውይይት አካል በሚያደርግዎት የአገር ጉዳይ ይሳተፉ።
ተወያዮች፡- የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀ መንብሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን ናቸው።
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5