የኢትዮ-ቴሌኮም መግለጫ

በትግራይ ክልል መቀሌ፣ ውቅሮ፣ ዓዲግራትና ዕዳጋ ሃሙስ አካባቢዎች የስልክ፣ መቀሌ ውስጥ ደግሞ የኢንተርኔትም አገልግሎቶችን እንደገና ማስጀመሩን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ።

ክልሉ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት በተቋማቱ ላይ የደረሰውን ጉዳይ ጠግኖ አገልግሎቶቹን ለማስቀጠል ጥረቶች መቀጠላቸውን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

ባለፉት 6 ወራት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው የሰላም ችግር ድርጅቱ ለማሳካት ካቀደው ዕቅድ 95% ብቻ ማሳካቱን ወ/ት ፍሬህይወት ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮ-ቴሌኮም መግለጫ