የኢትዮ-ቴሌኮም መግለጫ

  • መለስካቸው አምሃ
    በትረ ሥልጣን

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ

በኢትዮጵያ የሰሜን ክልል የቴሌኮም አገልግሎት የተቋረጠው ከተቋሙ ውጭ በሆኑ አካላት በተለያዩ ጣቢያዎቹ ላይ በተፈጸሙ የማሰናከል ድርጊት ነው ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ በአገሪቱ የተለያዩ ተቋማት ላይ ወደ 40 ቢሊዮን ያህል ጊዜ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መፈፀሙን የዘረዘረው የኢትዮ ቴሌኮምን መግለጫ ሕወአትን በጥፋቱ አውተንጣኝነት ወንጅሏል።

የጥቃት ሙከራዎቹ በመንግስት ተቋማት፣በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በመገናኛብዙሃን እና በቴሌኮምመሰረት ልማት ላይ የተነጣጠሩ እንደነበሩም መግለጫው አብራርቷል።

በትግራይ ክልል ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ጥረት ላይ መሆኑንም ኢትዮ-ቴሌኮም ጨምሮ አመልክቷል።

አድማጮች የኢትዮ-ቴሌኮምን መግለጫ ተንተራሶ የተጠናከረ ዘገባ በዜ መጽሄት ክፍለ ጊዜ ይቀርባል።

በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚው መግለጫን ተከትሎ ከህወሓት በኩል ምላሽ ለማግኘት ባደረግነው ጥረት፣ ቀደም ሲል የትግራይ ክልል አማካሪ የነበሩትንና አሁን ኒው ዮርክ የሚገኙትን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በሌሎች ሀገሮች እስከ አምባሳደርነት ያገለገሉትን አምባሳደር ፍስኃ አስገዶምን አነጋግረናቸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮ-ቴሌኮም መግለጫ