“ከሱዳን ወደ መተማ የሚገቡ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው” አይኦኤም

Your browser doesn’t support HTML5

“ከሱዳን ወደ መተማ የሚገቡ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው” አይኦኤም

ካለፈው ዐርብ እስከ ማክሰኞ በነበሩት አምስት ቀናት ብቻ፣ ከ3ሺሕ500 በላይ የ35 ሀገራት ዜጎች፣ የሱዳኑን ግጭት በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ የድንበር ከተማ መተማ መግባታቸውን፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ።

መተማ ከደረሱት ሰዎች መካከል የሚበዙቱ፣ የቱርክ ዜጎች እንደኾኑ የጠቀሱት፣ በኢትዮጵያ የአይኦ ኤም ቃል አቀባይ ኬ ቪራይ፥ የዩጋንዳ፣ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳንና የቻይና ዜጎች ደግሞ እንደ ቅደም ተከተላቸው ተከታዮቹን ደረጃዎች እንደሚይዙ አመልክተዋል።

አይኦኤም፣ ወደ 700 የሚጠጉ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎችን የመቀበል እና የማጓጓዝ ድጋፍ እንዲያደርግ፣ ከኤምባሲዎች በርካታ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት የገለጹት ኬ ቪራይ፣ ያንንም እያከናወነ መኾኑን አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡