ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን የመንፈቀ ረመዳን ኢፍጣር መርሐ ግብር አካሔደ

Your browser doesn’t support HTML5

ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን የመንፈቀ ረመዳን ኢፍጣር መርሐ ግብር አካሔደ

ሙስሊሞችን ለማገዝና በዓላትን በኅብረት ለማክበር ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የተመሠረተው ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን፣ ባለፈው ቅዳሜ፣ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የረመዳን ጾም አጋማሽ የኢፍጣር መርሐ ግብር አድርጓል።

ዝግጅቱ ለዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ለሚገኙ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ማኅበረሰብ ምስጋና ለማቅረብም መዘጋጀቱን ፋውንዴሽኑ ገልጿል፡፡ ይህም፣ ባለፉት ጥቂት ወራት ከማኅበረሰቡ በተሰበሰበው የ1ነጥብ8 ሚሊዮን ዶላር መዋጮ፣ ለመስጂድ እና ለትምህርት ቤት አገልግሎት የሚውል ሰፊ መሬት ለመግዛት ከመቻሉ ጋራ የተያያዘ እንደኾነ፣ የፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን የቦርድ ፕሬዚዳንት ጀማል ያሲን አስረድተዋል።

ኤደን ገረመው፣ ከ39 ዓመታት በፊት በተመሠረተው ፋውንዴሽን ባካሔደው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ተገኝታ ያሰናዳችው ዘገባ በመቀጠል ይቀርባል።