የኢትዮ-ግብፅ ስብሰባ አዲሳባ ላይ እየተካሄደ ነው - /ሪፖርት - በአዲስና ተጨማሪ መረጃ የታደሰ/

  • እስክንድር ፍሬው
“በዚህ ኃላፊነት ላይ ከተቀመጥኩ ጊዜ ጀምሮ በየወሩ ማለት በሚቻል ፍጥነት ወደ አዲስ አበባ እመላለሳለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ሁለታችንም ከፕሬዚዳንት አብዱል-ፈታህ ኤል-ሲሲና ከወንድማቸው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በየጊዜው መገናኘታችንን ጠንክረን እንድንቀጥል፣ የግንኙነታችንን መንፈስም ይዘን እንድንጓዝ በተቀበልነው መመሪያ መሠረት ነው፡፡” - ሳምሃ ሹክሪ - የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያና የግብፅ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ አዲሳባ ላይ እየተካሄደ ነው /ድምፅ - በአዲስ መረጃ የታደሰ/

በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ያሉ ግንኙነቶችን ለማሻሻል ያለሙ ተከታታይ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ሲሉ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳምሃ ሹክሪ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ የሚገኙት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው አቻቸው ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ዛሬ ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋርም ተወያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያና የግብፅ የጋራ ኮሚሽን የኤክስፐርቶች ስብሰባ ትናንት ተካሂዷል፡፡ ነገ ደግሞ ሌሎችም የሁለቱም ሃገሮች ሚኒስትሮች ይገኙበታል የተባለና በኢትዮጵያ በግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚመራ ከፍተኛ ስብሰባ ነገ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ሚስተር ሹክሪ አሁን ያሉበትን ኃላፊነት ከተረከቡ ወዲህ ወደአዲስ አበባ በየወሩ ማለት ለሚቻል ጊዜ እየተመላለሱ መሆኑን ጠቁመው ይህም እየተደረገ ያለው በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል-ፋታህ ኤል-ሲሲ እና “ወንድም” ብለው በጠሯቸው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መመሪያ መሠረት መሆኑን ገልፀዋል፡፡