ዋሺንግተን ዲሲ —
"ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቻችንን እንወዳለን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እና ውንጀላዎችን አሳሳች መረጃዎችን መደገፍ ትታችሁ በእውነተኛ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ ይኑራችሁ" በካልጋሪው ሰልፍ ላይ በአንድ ተሳታፊ በንባብ የተሰማ።
በትናንትናው ዕለት በካናዳ ከተሞች ከታካሄዱት ሰልፎች የካልጋሪው
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን “የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በሃሰት ፕሮፖጋንዳዎች ተመርተው በኢትዮጵያ ላይ አሉታዊ ጫና እያደረጉ ነው” ያሉትን በመቃወም ተመሳሳይ ሰልፎችን አካሂደዋል።
ትላንት ከቀትር በኋላ በበርካታ የካናዳ ከተሞች ስለ ተካሄዱት ስለ እነኚህ ሰልፎች ዓላማ እንዲያስረዱን ሰላማዊ ሰልፎቹን ካስተባበሩት የማሕበረሰብ ድርጅቶች የአንዱ ቃል አቀባይ የሆኑትን ዶ/ር ሰለሞን ምትኩን ሰልፎቹ በመካሄድ ላይ ባሉበት ወቅት በስልክ አግኝተን አነጋግረናቸዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በትውልደ ኢትዮጵያ-ካናዳውያን በበርካታ ከተሞች የተካሄዱት ሰልፎች