ፓርቲዎች በአገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ እየጠየቁ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

ፓርቲዎች በአገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ እየጠየቁ ናቸው

የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገራዊ ምክክር የሚሆኑ አጀንዳዎችን እንዲያዘጋጁ ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው፣ በሒደቱ ለመሳተፍ መተማመንን ያዳብራሉ ያሏቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

ከቅድመ ሁኔታዎቹ መካከል፣ በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩና በምክክር ሒደቱ የጎላ ሚና ሊኖራቸው ይችላል ያሏቸው አካላት እንዲፈቱ የሚጠይቁ ይገኙበታል፡፡

ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ ሒደቱ ኹሉንም አካላት ማሳተፍ ያለበት በመኾኑ፣ የፓርቲዎች ቅሬታ እልባት እንዲያገኝ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡