ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ ምርጫ፤ ቀን ተቆረጠ፤ ቅሬታ አቅራቢው ኮሚቴ ተቃውሟል

  • እስክንድር ፍሬው
በኢትዮጵያ መላውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በቀጥታ የሚያሣትፍ ምርጫ ለማካሄድ የጊዜ ሠሌዳ መውጣቱን የኢትዮጵያ ዑለማዎች ምክር ቤት አስታወቀ።

የሙስሊሙን ቅሬታ ለማቅረብ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አቡበከር አህመድ መሃመድ ግን ምርጫው አሁን ባሉት አመራሮች ሳይሆን በገለልተኛ አካል ካልተካሄደ እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።

ምርጫው አሁን እንደታሰበው በቀበሌዎች ሳይሆን በየመስጊዶቹ መካሄድ እንዳለበትም ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)