የሰሜን አፍሪቃን ሕዝባዊ መነሳሳት ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ያነፃፀረው ጋዜጠኛ በፈዴራሉ ፖሊሶች ወከባና እሥራት እንደደረሰበት ገለፀ።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዳስረዳው ባለፈው ሣምንት ስድስት በከባዱ የታጠቁ ፖሊሶች በትራፊክ በተጨናነቀችው መሃል አዲሳባ ውስጥ ከመኪናቸው ዱብ ዱብ ይላሉ። ወዲያው እያዋከቡና እያጣደፉ ወደ ማዕከላዊ ፖሊስ ለምርመራ ይወስዱታል። በምርመራ ማዕከሉ በታሠረባቸው ሁለት ሰዓታት ማንነታቸውን ካልገለፁት ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነር ፊት ቀርቦ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤ «የምታደርገው ሁሉ ፀረ-መንግሥት እንቅስቃሴ ነው» የሚል።
" ኢንተርኔት ላይ ባቀረብካባቸው ፅሑፎች ለተለያዩ መገናኛ አውታሮች በሰጠሃቸውም ቃለ-ምልልሶች ኢትዮጵያም ውስጥ ግብጽና ቱኒዝያን መሰል አመፅ እንዲጀመር ለመቀስቀስ ሞክረሃል፤ አሉኝ። አክለውም እንደዚያ ዓይነት ሁኔታ እዚህ አገር ውስጥ ሊከሰት እንደማይችልም ነገሩኝ።" ብሏል እስክንድር፡፡
ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡