የሱዳንና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በሰጡት ንግግር በየሃገራቸው የተጣለባቸውን የኢኮኖሚና የጦር እገዳ እንዲነሳላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ኦስማን ሳልህ የሃገሪቱን ድንበር እንዲክበርና ሕጋዊ አካሄድ እንዲሰፍር ለድርጀቱ አባሎች ገልጸዋል። የሱዳን ውጭ ጉዳን ሚኒስተር ኢብራሂም አህማን እብደል ዓዚዝ ጋንዶር በበኩላቸው ሰዎችን በማሸጋገር ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎችንና ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለማቆምና ወንጀለኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ እንደሚጥሩ ቃል ገብተዋል።
የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ የኤርትራ ድንበር እንዲክበርና ሕጋዊ አካሄድ እንዲሰፍን ለድርጀቱ አባሎች ደግመው ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው አርብ እለት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ኢብራሂም አህማን እብደል ዓዚዝ ጋንዶር በበኩላቸው በሃይል የሚጣል የኢኮኖሚና ናየጦር እቀባ ሱዳን እንደምትቃወም ገልጸው ሰዎችን በሕገ-ውጥ በማሸጋገር ተግባር ላይ የተሰማሩ ወንጀለኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ እንደሚጥሩ ቃል ገብተዋል።
ሳሌም ሰለሞን በኒው ዮርክ ከተማ ተገኝታ ያቀናበረችውን ዘገባ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5