ኤርትራ ውስጥ የአንድ የፖለቲካ እሥረኛ ሞት በሃገሪቱ የድብቅ እሥር ቤቶች ሥርዓት ላይ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ምክንያት እንደሆነ ተዘገበ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ኤርትራ ውስጥ የአንድ የፖለቲካ እሥረኛ ሞት በሃገሪቱ የድብቅ እሥር ቤቶች ሥርዓት ላይ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ምክንያት እንደሆነ ተዘገበ።
የሃገሪቱ መንግሥት በምሥጢር ይዟቸዋል በሚባሉ እሥር ቤቶች ውስጥ ከ16 ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ የመንግሥቱ መሥራች የሆኑ ፖለቲከኞች ሁሉ ታስረው እንደሚገኙ ተገልጿል።
በኤርትራ የነፃነት ውጊያ ወቅት ታጋይ የነበሩት ኃይሌ ወልደተንሣይ ከድብቅ እሥር ቤቶቹ በአንዱ ውስጥ መሞታቸው ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛዎች እየተነገረ ነው።