የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሶማልያና ኬንያ ሪፖብሊኮች የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ባለፈው ቅዳሜ ወደ ሀገራቸ ተመልሰዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሶማልያና ኬንያ ሪፖብሊኮች የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ባለፈው ቅዳሜ ወደ ሀገራቸ ተመልሰዋል።
ከኬንያው ርዕሰ ብሄር ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ግንኑነታቸውን ስለማጠናከርና ሁለቱን ሀገሮች ስለሚጠቅም የክልላዊ እደገት እንደተነጋገሩ ተዘግቧል። በሁለቱም ሀገሮች መካከል ያለውን የትብብር ዕድል መሰረት በማድረግ በንግድና በመዋዕለ-ነዋይ ዘርፎች አጋርነት እንዲዳብር ለመስራት ተስማተዋል። በሶማልያ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ለመጣርም ተስማምተዋል ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ባቀረቡት ግብዣ መሰረት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመጪው ጥር ወር ኤርትራን ይጎበኛሉ።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዛሬ ደግሞ አቡ ዳቢ ሄደው ከአልጋወራሽ ሼኽ ሞሐመድ ቢን ዛይድ ጋር ተገናኝተዋል።