የኒውዮርክ Grand Jury ውሳኔና ምላሹ!

  • ሰሎሞን ክፍሌ
አንድ ነጭ ፖሊስ ባልታጠቀ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ግድያ ወንጀል እንዳይከሰስ የኒውዮርክ Grand Jury የደረሰበት ውሳኔ፥ የተቃውሞ ሰልፍና የፌዴራሉን ፍርድ ቤት ምርመራ አስከትሏል።

Your browser doesn’t support HTML5

የኒውዮርክ Grand Jury ውሳኔና ምላሹ!

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ቁጥራቸው የበዛሰዎች በከተማዋ ዋና ዋና አደባባዮች ተሰባስበውታይተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፍትሕ ሚኒስቴር፥ ነጩ የፖሊስ መኮንንDaniel Pantaleo በወቅቱ መሳሪያ ያልታጠቀውንናባነስተኛ ወንጀል የተጠረጠረውን ጥቁር አሜሪካዊ Eric Garnerን በቁጥጥር ስር ያዋለው የሲቪል መብቶቹን በመጣስየማነቅ ዘዴ ተጠቅሞ መሆን አለመሆኑን አጣራለሁ ብሏል።

Garner በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ ጥቂት ጊዜ በሗላ ሕይወቱያለፈው የደረቱ ውስጥ የደም ፍሰት በመታመቁ ስለሆነየነፍስ ግድያ ወንጀል ነው ሲል የኒውዮርክ አስከሬን መርማሪቡድን ደምድሟል።