የቱርክ ፕሬዚዳንት በሞስኩ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፡ -የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋንና የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

ፎቶ ፋይል፡ -የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋንና የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን - ከሩሲያው አቻቸው ከቭላዲሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በአሁኑ ወቅት ሞስኩ ይገኛሉ።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን - ከሩሲያው አቻቸው ከቭላዲሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በአሁኑ ወቅት ሞስኩ ይገኛሉ።

ጉብኝታቸው እየተካሄደ ያለው የቱርክ ኃይሎች በሦሪያ ኩርድ ሚሊሽያዎች ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ለመክፈት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት ነው።

“እኛ ከ30 ዓመታት በላይ በዜጎቻችን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከሚፈፅም አሸባሪ ቡድን ጋር እንዴት መዋጋት እንዳለብን ከማንም ምክር አንጠይቅም ወይም ፍቃድ አንሻም” ሲሉ ኤርዶዋን ባለፈው ሣምንት በዕለታዊው ኮሜርሣንት - የሩሲያ ጋዜጣ ላይ አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

አንካራ “ዋይፒጂ” በመባል የሚታወቀውን የሦሪያ ኩርድ ሚሊሽያ እና ቱርክ ግዛት ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን “ፒዋይዲ” የሚል መጠሪያ የተሰጠውን የፖለቲካ ሸሪኩን የሽብር ድርጅቶች ናቸው ትላለች።

ሞስኩ እና አንካራ በሦሪያው የርስ በርስ ጦርነት ሁለት የተለያዩ ተቀናቃኝ ወገኖችን እንደሚረዱ ይታወቃል።

ኤርዶዋንና ፑቲን በአውሮፓውያኑ ዓመት 2018 በተለይ ሦሪያን አስመልክቶ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር 7 ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን 18 የቴሌፎን ጥሪዎችን ተለዋውጠዋል ተብሏል።