ሳዑዲ አረብያ የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢን አስከሬን የት እንዳደረሰች እንድትናገር ቆንስላዋ ውስጥ ከተገደለ በኋላ አስከሬኑን በማስወገድ ረገድ የረዷዋትን “የሃገር ውስጥ ተባባሪዎች” ያሏቸውን እንድታስታውቅ የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን ጠየቁ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሳዑዲ አረብያ የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢን አስከሬን የት እንዳደረሰች እንድትናገር ቆንስላዋ ውስጥ ከተገደለ በኋላ አስከሬኑን በማስወገድ ረገድ የረዷዋትን “የሃገር ውስጥ ተባባሪዎች” ያሏቸውን እንድታስታውቅ የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን ጠየቁ፡፡
ኤርዶዋን በሀገሪቱ ፓርላማ የኤኬ ፓርቲያቸው ተወካዮች ጉባዔ ላይ ባሰሙት ንግግር ስለጋዜጠኛው አገዳደል ዝርዝር ውስጥ ሳይገቡ ተጨማሪ ማስረጃ በእጃችን አለ ብለዋል።
የሳዑዲ አረብያ ጠቅላያ አቃቤ ህግ ከምርመራው በተያያዘ ከአንካራ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር የፊትችን ዕሁድ ይገባሉ ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ሳዑዲ አረብያ ትናንት ባወጣችው መግለጫ ከቱርክ በተገኙ መረጃዎች መሰረት ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢን የተገደለው አስቀድሞ በተቀባበረ መንገድ መሆኑን አምንለች። አሁን የቀረው ማነው አስቀድሞ ግድያዎን ያቀነባበረው የሚለው ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ጨምሮ ዓለምቀፍ ተቺዎች የመጨረሻው ኃላፊነት የሚያርፈው አልጋ ወራሹ መሃመድ ቢን ሳልማን ላይ እንደሚሆን እየተናገሩ ነው።