ኢሕአዴግ ጉባዔውን አጠናቀቀ

  • ግርማይ ገብሩ

አሥረኛው የኢሕአዴግ ጉባዔ በመቀሌ

አሥረኛው የኢሕአዴግ ጉባዔ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝን ሊቀመንበር፤ አቶ ደመቀ መኮንንን ምክትል አደርጎ መርጧል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ኢሕአዴግ ጉባዔውን አጠናቀቀ

አሥረኛው የኢሕአዴግ ጉባዔ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝን ሊቀመንበር፤ አቶ ደመቀ መኮንንን ምክትል አደርጎ መርጧል፡፡

ጉባዔው ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቶ ተጠናቅቋል፡፡

“በሃገሪቱ እየተመዘገበ ያለውን ፈጣን ዕድገት ከሕዝቡ ጋር በመሆን እንቀጥላለን” ብሏል አሕአዴግ፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትም የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርጉም አባላቱ መናገቸው ተጠቅሷል፡፡

ሊቀመንበሩ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ በምርጫ ተፎካካሪ ከነበሩ ድርጅቶች ጋር ኢሕአዴግ በሕጋዊና በሠላማዊ መንገድ ለመሥራት እንደሚተባበርም ገልፀዋል፡፡

የአረና መድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገብረሥላሴ ጥሪው እንደተለመደው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የተደረገ ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡