እንግሊዝ እና ስፔን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በሴቶች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ለመሳተፍ በቅተዋል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒዎኗ እንግሊዝ ለዋንጫው ጨዋታ የበቃችው፣ ከኒውዚላንድ ጋራ የሴቶች የዓለም ዋንጫን በማስተናገድ ላይ የምትገኘውን አውስትራሊያን፣ 3 ለ 1 በኾነ ውጤት፣ ዛሬ በማሸነፏ ነው።
ዋንጫውን ለማንሣት፣ እንግሊዝ እና ስፔን፣ የመጨረሻውን ፍልሚያ፣ በዕለተ እሑድ ያደርጋሉ።
አውስትራሊያ እና ስዊዲን፣ ለሦስተኛ ደረጃ የሚያደርጉትን ጨዋታ፣ በዕለተ ቅዳሜ ያከናውናሉ።