በሴኔጋሉ ምርጫ ዛሬ ሐሙስ ይፋ በሆነው ጊዜያዊ ውጤት መሠረት፣ ማኪ ሳል እንደገና አሸናፊ ሆነዋል።
የሴኔጋል ምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቁት፣ በእሑዱ ምርጫ፣ የ57 ዓመቱ ማኪ ሳል፣ 58% በሆነ ድምፅ የመሪነቱን ስፋራ ይዘዋል። ተቀናቃኛቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እድሪስ ሰኬ ደግሞ በ21% ድምፅ ይከተላሉ።
አሁን የተገኘው ውጤት በህገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ከተደገፈ፣ ሳል፣ የመጀመሪያ ዙር አሸናፊ ይሆናሉ። ተቀናቃኞቻቸው ግን ሌላ ዙር ውድድር እንደሚያስፈልግ ነው የሚናገሩት።
ሴኔጋል፣ የተረጋጋ ዴሞክረሲ ከሚካሄድባቸው የአፍሪካ አገሮች አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡