የቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ

  • እስክንድር ፍሬው

edp press conference

ቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ለሚያስችል ጊዜ መራዘም እንዳለበት በአቶ አዳነ ታፈሰ የሚመራው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ አሳሰበ።

ምርጫው “በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ነው” ያላቸውን የፖለቲካ ኃይሎች ተችቷል።

እነዚህ ኃይሎች “ሰላማዊ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ በሚካሄድ ምርጫ ለሥልጣን ለመብቃት የተሻለ ዕድል እንዳላቸው የሚያምኑ ናቸው” ብሏል።

የምርጫ ጊዜን የማራዘም ሥልጣን “የእኔ አይደለም” ያለው ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ “ምርጫው በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል” በሚል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለቪኦኤ አስታውቋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ