“የዓመቱ ፈርጦች” - የዘንድሮው የኢትዮጵያ-አሜሪካውያን ማኅበር ተሸላሚዎች

Your browser doesn’t support HTML5

“የዓመቱ ፈርጦች” - የዘንድሮው የኢትዮጵያ-አሜሪካውያን ማኅበር ተሸላሚዎች

31ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው፣ የሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን - አሜሪካውያን የሽልማት ድርጅት - ማኅበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጵያ፣ ዘንድሮም፥ “የዓመቱ ምርጦች” ላላቸው ተሸላሚዎቹ፣ በዋሽንግተን ዲሲ መውጫ የኮሌጅ ፓርክ ከተማ በደማቅ ሥነ ሥርዓት አክብሮት ሰጥቷል።

በአዋቂዎች ጎራ፡- ሰባት ግለሰቦች እና ሁለት የማኅበረሰብ ድርጅቶች፤ በአዳጊ ወጣቶች ጎራ ደግሞ፣ በትምህርታቸው ባስመዘገቡት የላቀ ውጤት እና በከፍተኛ ማኅበራዊ ተሳትፎዎቻቸው በብሔራዊ ደረጃ የተመረጡ ስምንት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ለዘንድሮው የድርጅቱ አክብሮት በቅተዋል፡፡