የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በህወሓት ታጣቂዎች ላይ የቀረቡ ክሦችን እንደሚመረምር አስታወቀ

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በህወሓት ታጣቂዎች ላይ የቀረቡ ክሦችን እንደሚመረምር አስታወቀ

የህወሓት ታጣቂዎች በተለያዩ የአማራና የአፋር ክልሎች አካባቢዎች ውስጥ “ከባድ ሊባሉ የሚችሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለመፈፀማቸው አቤቱታዎች እንደደረሱት” የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።

ምርመራ እና የማጣራት ሥራ እንደሚያከናውኑ ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ሰሞኑን በተቆጣጠራቸው የአማራና የአፋር አካባቢዎች “በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች በህወሓት ታጣቂዎች መገደላቸውንና በርካታ ሴቶች መደፈራቸውን” የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ሰሞኑን ገልፆ ነበር።