በጋምቤላ ክልል ዐያሌዎች የተገደሉበት የብሔር ግጭት የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ ኢሰመኮ አሳሰበ

Your browser doesn’t support HTML5

በጋምቤላ ክልል ዐያሌዎች የተገደሉበት የብሔር ግጭት የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ ኢሰመኮ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ ብሔርተኛ ታጣቂ ቡድኖች፣ በልዩ ልዩ የክልሉ ወረዳዎች በፈጸሙት ጥቃት፣ በርካታ ንጹሐን ሰዎች እንደተገደሉ አስታወቀ፡፡ በጥቃቱ ምክንያት፡- የአካል ጉዳት፣ የነዋሪዎች መፈናቀል እና የንብረት ውድመት መድረሱንም አመለከተ።

የተቋሙ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ በመግለጫው ዙርያ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ በወንዞች ሙላት ምክንያት፣ በግጭቱ የተጎዱ ሰዎች፣ ወደ ሕክምና መስጫ ተቋማት ሳይደርሱ፣ በየመንገዱ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋል፡፡ በጋምቤላ ክልል ያለው የጸጥታ ኹኔታ፣ እያደረሰ ካለው ከፍተኛ ጉዳት እና የመብቶች ጥሰት አንጻር፣ የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት እንደሚፈልግ፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።