አዲስ አበባ —
በጋምቤላ ክልል እስር ቤቶች የመብት ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ።
በጋምቤላ ክልል በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይም እስርና እንግልትን ጨምሮ የአባላት ቤተሰቦችም ከመንግሥት ሥራ እስከመታገድ የሚደርስ በደል እንደሚደርስባቸው ኮሚሽኑ ገለፀ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከታኅሣሥ 12 እስከ ታኅሣሥ 15 ድረስ በጋምቤላ ከተማና በአኝዋክ ዞን ያደረገውን ጉብኝት ጠቅሶ ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው የጽሑፍ መግለጫ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ሰዎች አያያዝና ሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ በአፋጣን ሊሻሻል እንደሚገባው አሳስቧል።
በጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት ከታኅሣሥ ወር መግቢያ ጀምሮ በኦነግ ሸኔነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሁለት የ11 እና 1ዓመት ህፃናት ወንዶች እንዲሁም የ14 ዓመት ሕፃን ሴት ከእስር እንዲለቀቁ እና በሕፃናቱ ላይ ድብደባ ያደረሱባቸው የፀጥታ አባላት ላይ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግባቸው አሳስቧል።
በአብዛኛው የትግራይ ተወላጅ የሆኑ 90 ሰዎች በክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5