አምቦ —
አሶሺየትድ ፕረስ በኢትዮጵያ የሚገኘው የቪዲዮ ዘጋቢው በአዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ መያዙን አስታወቀ።
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች መንግስት ያሉበትን ሁኔታ እንዲያሳውቅ ያሳሰበ ሲሆን ዓለም አቀፉ የሲፒጄ የተባለ ለጋዜጠኞች መብት የሚቆመው ድርጅት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጠቀም የፕሬስ አባላትን ከማሰር ትቆጠብ ሲል መግለጫ አውጥቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ "ጋዜጠኛው የሸኔን እንቅስቃሴ ለዓለም ህዝብ ለማሰተዋወቅ በመስራቱ ነው የታሰረው፤ እርሱና ባልደረቦቹ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ነው የታሰሩት" ሲል አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ሚድያና ኮምኒኬሽን ሀላፊ አቶ ጄይላን አብዲ የሲፒጄን መግለጫ ሀሰት ነው ሲሉ በማጣጣል፣ ኢሰመኮ ያሳሰባቸው ጉዳዮችም ቢሆኑ "በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከሉ ናቸው" ሲሉ ለቪኦኤ ገልጸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5