በልዩ ኃይሎች “መልሶ ማደራጀት” ትግበራ ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁ ኢሰመኮ አሳሰበ

  • መለስካቸው አምሃ

Your browser doesn’t support HTML5

በልዩ ኃይሎች “መልሶ ማደራጀት” ትግበራ ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁ ኢሰመኮ አሳሰበ

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የክልሎች ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የጀመረው ፕሮግራም፣ ሰብአዊ መብቶችን አደጋ ላይ በማይጥል አሠራር እንዲተገበር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

በዐማራ ክልል፣ የመልሶ ማደራጀቱን ውሳኔ በመቃወም በተፈጠሩ ግጭቶች የደረሱ ጉዳቶችን ከመከታተል እና ከመመርመር ሥራው ጎን ለጎን፣ ችግሮቹ በውይይት የሚፈቱባቸውን ምክረ ሐሳቦች፣ በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የመንግሥት ሓላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በመስጠት፣ የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ፣ ኮሚሽኑ በአወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአገሪቱ የሚስተዋለው ነባራዊ ኹኔታ የፈጠረው ስጋት እና ያለመተማመን ስሜት፣ የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ጸጥታ ተቋማት ለማስገባት ከተላለፈው ውሳኔ ጋራ ተያይዞ፣ በክልሉ ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ እና ለተፈጠረው ግጭት መንሥኤ መኾኑን ያብራራው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ የሚወሰዱ ርምጃዎች፣ ሰላማዊ እና ሕጋዊ መኾን እንደሚገባቸው አሳስቧል፡፡

የኮሚሽኑን የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ክፍል ከፍተኛ ዳይሬክተር አነጋግረናል፡፡

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።