በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ውስጥ አገልግሎቱን እያስፋፋ ያለው - “ተድላ አምቡላንስ”

አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ

አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ

Your browser doesn’t support HTML5

በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ውስጥ አገልግሎቱን እያስፋፋ ያለው - “ተድላ አምቡላንስ”

አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፣ ኑሯቸውን በአሜሪካ በማድረግ፣ በሕክምና ትራንስፖርት ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡

በሪችመንድ ቨርጅኒያ የጀመሩት፣ ድንገተኛ ላልኾኑ የሕክምና አገልግሎቶች የአምቡላስ አገልግሎት የሚሰጠው ድርጅታቸው፣ ዘጠኝ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲኾን፣ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን ወደ አላባማ እና ሰሜን ካሮላይን እያሰፉ መኾኑን ይናገራሉ፡፡

ከ40 በላይ ኢትዮጵያውያን በድርጅታቸው ውስጥ አብረዋቸው እንደሚሠሩ አቶ ሳሚ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያም ድርጅቱን “ተድላ አምቡላስ” በሚል ሰይመው በዐዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ያስታወቁት አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፣ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም እያስፋፉት እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡