የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ የካይሮ ጉብኝት

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን፤ በካይሮ፣ ግብፅ

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን፤ በካይሮ፣ ግብፅ

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ትናንት ዕሁድ በካይሮ ፕሬዚዳንታዊ ቤተመንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብፅን ከፍተኛውን የክብር ኒሻን አበርክተውላቸዋል፡፡ሁለቱ አገሮች በርካታ ስምምነቶችን የተፈራፈሙ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የንግድ ትብብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተመልክቷል፡፡

ከዓለም ትልቅ የህዝብ ቁጥር ያላት ህንድ፣ ያልተጣራ የነዳጅ ድፍድፍ፣ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ፣ ጨው እና ጥጥን ጨምሮ፣ የግብፅን ምርቶች ተቀባይ ከሆኑ አምስት አገሮች መካከል አንዷ ናት፡፡

ግብፅም በበኩሏ ህንድ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ዋነኛ ምርቶች መካከል፣ የጥጥ ክርን፣ ቡናን፣ ዕጽዋት፣ ትምባሆ፣ ምስር፣ የተሽከርካሪ ክፍሎች፣ መርከቦች፣ ጀልባዎችና የኤሌክትሪክ ማሽኖች ታስገባለች፡፡

ባላፈው ቅዳሜ ካይሮ የገቡት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፣ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በኋላ ግብፅን ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙ የህንድ መሪ ናቸው፡፡

ሞዲ ግብሽን የጎበኙት የግብፁ መሪ ኤል ሲሲ በህንድ የነጻነት በዓል ላይ በክብር እንግድነት በኒውደልሂ ከተገኙ 6 ወራት በኋላ መሆኑ ነው፡፡

ግብፅ እና ህንድ ጥልቅ ግንኙነት የጀመሩት፣ በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ፣ የገለልተኛ ንቅናቄ በመመስረት ቁልፍ ሚና ከተጫወቱባቸው እኤአ ከ1950ዎቹ ጀምሮ መሆኑም ተመልክቷል፡፡