የግብፅ የባቡር መስመር ባለሥልጣን ከሥራ ተባረሩ

  • ቪኦኤ ዜና

ካይሮ ግብፅ

ግብፅ ውስጥ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሦስት የባቡር አደጋዎች መከሰከሳቸውን ተከትሎ ዋናውን የባቡር መስመር ባለሥልጣን ከሥራቸው ተባረሩ።

በተከታታይ ባደረሱት አደጋዎች ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን ከሦስት መቶ ሃምሳ የሚበልጡ ቆስለዋል።

የግብፅ የትራንስፖርት ሚኒስትር የባቡር መስመሩን ዋና ሥራ አስኪያጁን ከሥራ ያባረሩዋቸው የተዳከመውን የድርጅቱን የአሰራር ስርዓት ለማስተካከል ነው ተብሏል።

ግብፅ ውስጥ በየዓመቱ በመቶዎች የተቆጠሩ የባቡር አደጋዎች የሚያጋጥሙ ሲሆን የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሥራ አስኪያጁን ያባረሩዋቸው ባለፈው ዕሁድ ከዋና ከተማዋ ከካይሮ አቅራቢያ የደረሰውንና ሃያ ሦስት ሰዎች መሞታቸው እና አንድ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸው ከተገለጸው አደጋ ተከትሎ መሆኑ ነው።