ኢትዮጵያ ያሉትን የማየው በጥንቃቄ ነው፤ ለማንኛውም በፀጋ እንቀበላለን ትላለች፡፡
ዋሺንግተን ዲ.ሲ.-አዲስ አበባ —
“የአባይ ውኃ ለግብፅ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው” ሲሉ የግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩና የቀድሞው የጦር ኃይሎቿ አዛዥ አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ተናግረው ከኢትዮጵያ ጋር ግን በመግባባት መሥራት እንደሚያስፈልግ በሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ በተላለፈ ቃለ-ምልልሳቸው ገልፀዋል፡፡
አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ደግሞ የኤል-ሲሲ ንግግር ከቀድሞዎቹ መሪዎች የተለየ ሆኖ እንዳላገኙት ገልፀው ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡና ያሉትን በተግባር ከፈፀሙ “ከግማሽ መንገድ በላይ ሄደን እንቀበላቸዋለን” ሲሉ ለቪኦኤ ማምሻውን አመልክተዋል፡፡
ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ሳይሆኑ አይቀሩም እየተባለ በስፋት የሚወራላቸው አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ካሳወቁ ወዲህ የመጀሪያውን የቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ላሚስ ኤል ሃዲዲ፣ እንዲሁም ኢብራሂም ኢሣ ከሚባሉ ጋዜጠኞች ጋር አድርገዋል፡፡
ኤል-ሲሲ ሲቢሲ ከሚባለው የግል ቴሌቪዥን ጣቢያና በተመሣሣይ ጊዜም ኦን-ቲቪ በሚባል ሌላ ጣቢያ በተሠራጨው ረዥም ቃለምልልሳቸው የተነተኑት የመጭ ፖሊሲያቸው ንድፍ የሚመስል ሃሣባቸውን ነው፡፡
የአባይ ወንዝ፣ የኅዳሴ ግድብና ከኢትዮጵያ ጋር ያሉ ግንኙነቶች ጉዳዮችም ተነስተዋል፡፡
ለዝርዝሩ ዘገባውንና በኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ ሙሉ ቃል የተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5