ኮቪድ 19 እና የአዕምሮ ጤና .. ሃሳብ ገብቶዎታል?.. ብቻዎን አይደሉም!

ፕሮፌሰር መስፍን አረአያ እና ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ

ያሉበት ሁኔታ - የጤና እና የኑሮ ብርቱ ፈተናዎች ያስጨንቁዎታል? .. ብቻዎን አይደሉም!

Your browser doesn’t support HTML5

ኮቪድ 19 እና የአእምሮ ጤና - ክፍል አንድ

የኮቪድ ቀጣይ ምዕራፎች እና ፈተናዎቹ:-

Your browser doesn’t support HTML5

ከዚህ ስንወጣ - ክፍል ሁለት

Your browser doesn’t support HTML5

ነገ .. የፊታችን መንገድ .. - ክፍል ሶስት

የኮረናቫይረስ መዛመድ የከሰተውን አሳሳቢ ሁኔታ ተከትሎ በእርስዎና በቤተሰብዎ፤ በወዳጅ የዘመዶችዎ አለያም በጉዋደኞችዎ፤ ብሎም በወገኖችዎ ጤና እና ደህንነት ጉዳይ ሃሳብ ገብቶዎታል? በኑሮዎ ላይ እያሳደረ ያለው ሊያሳድር የሚችለው ጫና እና መቃወስ ለጭንቀትና ለምን ይመጣ ይሆን ስጋት ዳርጎዎታል? ጭንቀትዎም ይሁን ስጋትዎ ምክኒያታዊ ነው።

አንዳንዴም ከዚህ አልፎ ግራ ግብት ይልዎ ይሆናል። አሳሳቢው ፈተናዎች መላ ፍለጋ በሃሳብም በአካልም የቻሉትን ያህል ደክሞም ቢሆን መፍትሄ በመሻት እና ለመንፈስ መረበሽ በመዳረግ መሃከል ግን ትልቅ ልዩነት አለ።

በእርግጥ እንዲህ ግራ የሚያጋባው ነገር በበዛበትና ሰማይ የተደፋ በሚመስልበት ጊዜ ራስን ከከፋው አደጋ ለመታደግ የሚያስችልና በተጨባጭ ሊደረግ የሚችል ነገር ይኖር ይሆን? ሁለት ታዋቂ የአንጎል ህክምና ባለሞያዎች ጋር በምናደርገው ደርዝ ያለው ወግ የችግሮቹን ተፈጥሮና መንሴዎች፡ ብሎም የተሻሉ አማራጮች በትልቀት እና በዝርዝር እንፈትሻለን። ከዚያም ሻገር ብለን የመጭውን ዘመን የነገውን ዓለም ህይወት ገጾች እንገልጣለን።

ተከታታይ ክፍል ውይይቶቹን ከዚህ ያድምጡ።