በዐማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የዘንድሮ ተመራቂዎች ዝውውር ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የዘንድሮ ተመራቂዎች ዝውውር ጠየቁ

በዐማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ የዘንድሮ ተመራቂዎች፣ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች እንዲዛውራቸው፣ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠየቁ፡፡

እንደ ትምህርት መርሐ ግብራቸው፣ “የ2016 ዓ.ም. ተመራቂዎች ነበርን፤” ያሉ ተማሪዎች፣ በወቅታዊው የዐማራ ክልል የጸጥታ ኹኔታ ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎቹ እስከ አኹን እንዳልጠሯቸውና ትምህርትም እንዳልተጀመሩ ገልጸው፣ “የመመረቂያ ሒደቱንና የመውጫ ፈተናውን ያወሳስብብናል፤” ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል እና በወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ እንደነበሩ የተናገሩት ተማሪዎቹ፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ትምህርታቸው የታጎለባቸው ተማሪዎች፣ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲማሩ መወሰኑን አስታውሰው፣ እነርሱም በውሳኔው መሠረት ዝውውር እንዲደረግላቸው፣ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ እና አስተያየት እንዲሰጡን፣ የእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ባለመነሣቱ ምክንያት ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።