የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ

  • እስክንድር ፍሬው
ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የተወሰኑ አመራሮችን ከኃላፊነት ዝቅ እንዲሉ መወሰናቸውን የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የተወሰኑ አመራሮችን ከኃላፊነት ዝቅ እንዲሉ መወሰናቸውን የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል። የፓርቲው ሊቀ መንበር ስለመሆናቸው የምርጫው ቦርድ ዕውቅና እንዳላቸው የተናገሩት ዶክተር ጫኔ ከበደና ሌሎች የሥራ አስፋፃሚ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው በብሔራዊ ምከር ቤቱ ያካሄደው እና እነሱ እንዲነሱ የወሰነበት ስብሰባ ህገወጥ አንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ትላንት የተካሄደው የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባና የአመራር ምርጫ ቃለ ጉባዔ እንደደረሰው አረጋግጧል። በአጭር ጊዜ ውስጥ መርምሮ ምላሽ እንደሚሰጥም አስታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ