በኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ማክተሙ ተነገረ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ የኢኩዌትር ክፍለ ግዛት የኢቦላ ወረርሽኝ ማክተሙን የዓለም የጤና ድርጅት ትናንት ይፋ አደረገ።

የመጀመሪያው የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ የተገኘው ከስድስት ወራት በፊት ሲሆን የሃገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት የቫይረሱ ስርጭት እጅግ አስደሳች ዜና ነው ብለዋል።

በጥቅጥቅ ደን በተሸፈነው እና ሰፊ በሆነው ክፍለ ሃገር ማኅበረሰቡን መድረስ ደግሞ እንዲያምኑን ማድረግ ፈታኝ ነበር ሲሉ ነው ያስረዱት።

ከዚያም በላይ ኮቪድ-19 ወርርሽኝን የመታገሉ ሥራ መጨመሩ ይበልጡን ስራችንን እክብዶት ነበር ሲል አብራርቷል።