ከቆቃ- ሁርሶ በተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል

በኢትዮጵያ፣ ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት፣ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ከቆቃ- ሁርሶ በተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል

በኢትዮጵያ፣ ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት፣ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

በዚህ ጉዳት ምክንያት፣ ለምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች እና አካባቢዎች፣ ለአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር መስመርና ለጅቡቲ የሚቀርበው ኅይል ተቋርጦ እንደነበር ያመለከተው ተቋሙ፣ አሁን ግን በሌሎች መስመሮች ኅይል እየቀረበላቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር በበኩሉ፣ በኤሌክትሪክ ሀይል መስመሮች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት፣ በአገልግሎቱ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡