በኪረሙ ከተማ ከተጠለሉ 62ሺሕ ተፈናቃዮች ገሚሱ እንደተመለሱ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በኪረሙ ከተማ ከተጠለሉ 62ሺሕ ተፈናቃዮች ገሚሱ እንደተመለሱ ተገለጸ

ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ የግጭት ተፈናቃዮች ከነበሩት 62ሺሕ ሰዎች መካከል፣ ከ25ሺሕ በላይ የሚኾኑ ወደ ቀዬአቸው እንደተመለሱ፣ የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ከወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ገና ካልተመለሱት መካከል ደግሞ፣ ላለፉት አራት ወራት ድጋፍ እንዳልደረሳቸውና ለችግር እንደተጋለጡ የገለጹ ይገኙበታል፡፡

የወረዳው የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት በበኩሉ፣ የቅሬታውን ተገቢነት ተቀብሎ ምላሽ እንዲያገኝ ለሚመለከተው አካል ማሳወቁን ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።