የበቴ ዑርጌሳን ግድያ ተከትሎ በባቱ እና መቂ ከተሞች በተቀሰቀሰ ግጭት ውጥረት መስፈኑ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የበቴ ዑርጌሳን ግድያ ተከትሎ በባቱ እና መቂ ከተሞች በተቀሰቀሰ ግጭት ውጥረት መስፈኑ ተገለጸ

በምሥራቅ ሸዋ ዞን በባቱ እና መቂ ከተሞች፣ በኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች እና በመንግሥት ኀይሎች መካከል፣ ሰሞኑን እንደጀመረ የተገለጸው የተኩስ ልውውጥ ዛሬም መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ።

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የባቱ ከተማ ነዋሪ፣ ካለፈው ሰኞ ምሽት እስከ ትላንት ማክሰኞ ጠዋት፣ በከተማዋ ቀጥሎ የነበረው የተኩስ ልውውጥ፣ ለእንቅስቃሴ መገደብ እና ለአገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ኾኗል፤ ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ምሽት፣ በዚያው በመቂ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት፣ አራት የነዳጅ ማደያ ጠባቂዎች ታግተው እንደተወሰዱ ተመልክቷል። በጉዳዩ ላይ፣ ከመንግሥት አካል ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።