በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ 3 ሲቪሎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

የኢትዮጵያ ካርታ

የኢትዮጵያ ካርታ

Your browser doesn’t support HTML5

በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ 3 ሲቪሎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ታጣቂዎች ባለፈው ማክሰኞ በከፈቱት ጥቃት 3 ሲቪሎች ተገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ከተገደሉት በተጨማሪ 3 ሰዎች መቁሰላቸውን እና የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈፀሙንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡

ጥቃቱ የተፈፀመው “ሸኔ” ሲሉ በገለፁት ታጣቂ ቡድን መኾኑን አመልክተው፣ ቢያንስ 400 አባወራዎች መፈናቀላቸውን እና በችግር ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ከመንግሥት በኩል አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዕማኛቹ "ሸኔ" በማለት የገለፁትና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በማለት የሚጠራው ቡድን ከዚህ ቀደም የቀረቡበበትን ተመሳሳይ ውንጀላዎች፣ ታጣቂዎቹ ሲቪሎችን እና የሲቪል ተቋማትን ኢላማ እንደማያደርጉ በመግለጽ አስተባብሏል።