በሺርካ ወረዳ ሃይማኖት የለየ በተባለ ጥቃት 36 ምእመናን ሲገደሉ ቀሪዎቹ እንደሸሹ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በሺርካ ወረዳ ሃይማኖት የለየ በተባለ ጥቃት 36 ምእመናን ሲገደሉ ቀሪዎቹ እንደሸሹ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ፣ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለ ማንነት ተኮር ጥቃት፣ 36 ምእመናን እንደተገደሉ፣ አንድ የስፍራው ነዋሪ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን ነዋሪው፣ ከሟቾቹ መካከል ዐሥር የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ስምንት የሌላ ቤተሰብ አባላት እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡

ሟቾቹ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንደኾኑና ጥቃቱም በሃይማኖታዊ ማንነት ላይ ያተኮረ እንደኾነ፣ ነዋሪው አክለው አመልክተዋል፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ጥቃቱን የፈጸመው፣ መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ የሚጠራው ዐማፂ ኃይል ነው፤ ብለዋል፡፡

በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” የተባለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ታርቢ ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።