Your browser doesn’t support HTML5
ትረምፕ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው በነበረው ስፍራ በድጋሚ ቅስቀሳ አደረጉ
ሊጠናቀቅ የአንድ ወር ጊዜ በቀረው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ፤ የዴሞክራቲክ እና የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪዎች ውጥረት የተሞሉባቸው ሳምንታት ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል፡፡
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሀሪስ ቁልፍ በሆኑ ግዛቶች ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ለማድረግ መርሃ ግብሮች ያሏቸው ሲሆን፤ ነገር ግን አንዳንድ ንግግሮች ጸብ አጫሪ እየሆኑ መምጣታቸውን አመላካች ነገሮች አሉ፡፡