Your browser doesn’t support HTML5
የዲሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ዛሬ ይጀምራል
ዛሬ ምሽት በሚጀምረው የዲሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ከየክፍለ ግዛቱ የተውጣጡ በሺሕ የሚቆጠሩ የፓርቲው ተወካዮች በቺካጎ ከተማ ተገኝተዋል።
ለአራት ቀናት የሚቆየው ብሔራዊ ጉባኤ፣ የፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ ካመላ ሄሪስ እና እጩ ምክትል ፕሬዝደንት ቲም ዋልዝ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንቶች ባራክ ኦባማ እና ቢል ክሊንተን እንዲሁም ታዋቂ የፓርቲው ዓባላት የሚያደርጉትን ንግግር ያደምጣል።
ጉባኤው በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ውሎ የፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ንግግር ያደምጣል።
የቪኦኤ ከፍተኛ የዋሽንግተን ዘጋቢ ካሮሊን ፕረሱቲ እንዲሁም ሌሎች የቪኦኤ ባልደረቦች የላኩትን ዘገባ ጨምቆ እንግዱ ወልዴ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።