Your browser doesn’t support HTML5
በዕጩ ፕሬዚዳንት ካማላ ሐሪስ ላይ የተነጣጠሩ ጾታ እና ዘር ተኮር ትችቶች
በዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሐሪስ ላይ፣ ጾታቸውንና የዘር ግንዳቸውን መሠረት ያደረጉ ትችቶች ሲሰነዝሩባቸው ይሰማሉ።
ተቺዎቹ፣ “በነጻው ዓለም፣ በግልጽም ኾነ በተዘዋዋሪ፣ ከኹሉም ከፍተኛ የኾነውን የሥልጣን ቦታ ሴት ልትይዘው አትችልም፤” ሲሉ፣ ሐሪስ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚያደርጉትን ፉክክር ይኮንናሉ።
የጾታዎች ጉዳይ ምሁራን ደግሞ፣ እነዚኹ የካማላ ሐሪስ ነቃፊዎች፣ ከሴትነታቸው በተጨማሪ በዘር መሠረታቸውም ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየሰነዘሩባቸው መኾኑን ይናገራሉ።