ካማላ ሐሪስ እና ዶናልድ ትረምፕ በኢሚግሬሽን ጉዳይ

  • ቪኦኤ ዜና

ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሐሪስ

በመጪው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ መራጮች ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጧቸው ጉዳዮች አንዱ የኢሚግሬሽን ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሐሪስ አቃቤ ሕግ ሆነው በሠሩባቸው ጊዜያት ስላከናወኗቸው ሥራዎች በማውሳት የምረጡኝ ዘመቻቸውን እያካሄዱ ናቸው፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ካማላ ሐሪስ እና ዶናልድ ትረምፕ በኢሚግሬሽን ጉዳይ

የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በበኩላቸው የባይደን ሐሪስ አስተዳደርን ሬኮርድ በመተቸት ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸውን ፍልሰተኞች በብዛት እንደሚያስወጡም ቃል በመግባት ላይ ናቸው። በአሊን ባኾስ የተጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡