የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃዎች፣ እንደ መትረየስ አከታትለው ጥይት እንዲተኩሱ የሚገጠመው ማቀባበያ ቃታ ጥቅም ላይ እንዳይውል የከለከለውን እገዳ፣ ባለፈው ሳምንት ቀልብሶታል።
Your browser doesn’t support HTML5
የአሜሪካ ድምፁ ስካት ስተርንስ ባጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመሣሪያ እና የመሣሪያ ባለቤትነት ጉዳይ፣ በመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዐቢይ ጉዳይ ኾኖ እንዲቀጥል ያደርጋል።
ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።