በመጪው ዓመት ኅዳር ወር፣ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በምታካሒደው ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጥላቻ እና አክራሪ አመለካከት ከአሁን ቀደም ባልታየ መልኩ እየተስፋፋ እንደኾነ፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ የወጣ ዐዲስ ሪፖርት አመለከተ፡፡
አሳታፊ የኾነውን የአገሪቱን የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመሸርሸር የሚሞክሩ የነጭ የበላይነት አቀንቃኞች፣ እንዲሁም LGBTQ+ በሚል ጥቅም መጠሪያ የሚታወቁትን የተለያየ ጾታዊ ዝንባሌ ያላቸውን ማኅበረሰቦች ጠል የኾኑ ቡድኖች መበራከታቸውን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
የቪኦኤዋ ቬሮኒካ ኤግሊሲያስ ባልዴራስ፣ በሪፖርቱ የተካተቱን ምርምሮች እና በምርጫው ላይ የሚኖራቸውን አንድምታዎች የዳሰሰ ዘገባ አስተላለፋለች፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡