ባይደንና ትረምፕ በቻይና ላይ ስለሚጥሉት ታሪፍ ይናገራሉ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ባይደንና ትረምፕ በቻይና ላይ ስለሚጥሉት ታሪፍ ይናገራሉ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በያዝነው ሳምንት፣ ከቻይና በሚገቡ በኤሌክትሪክ ኀይል በሚሠሩ ተሽከርካሪዎች፣ ብረት፣ የአልሙኒየም ውጤቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ አስተላላፊ (ሰሚኮንዳክተርስ) ላይ ታሪፍ እንዲጨመር አድርገዋል።

ርምጃው የተወሰደው፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በቻይና ላይ ይከተሉት የነበረውን የንግድ ፖሊሲ የባይደን አስተዳደር ከገመገመ በኋላ ነው፤ ተብሏል።

የቪኦኤ የኋይት ሐውስ ቢሮ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ፣ ሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ልዩነት ተመልክታለች፡፡ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።