በአፋር ክልል ሰሞኑን በጣለው ዝናብ ጥሩ ተስፋ እንዳገኙበት የዱብቲ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
አፋር ክልል፤ አዲስ አበባ —
Your browser doesn’t support HTML5
በአፋር ክልል ሰሞኑን በጣለው ዝናብ ጥሩ ተስፋ እንዳገኙበት የዱብቲ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ሆኖም ዝናቡ ቀጥሎ ሣር በደንብ እስኪያቆጠቁጥና እንስሳቱም መኖ እስኪያገኙ የመንግሥትም ሆነ የለጋሾችን እርዳታ እንደሚሹ ነዋሪዎቹ አካባቢውን እየተዘዋወረ እየተመለከተ ላለው ዘጋቢያች ግርማይ ገብሩ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በዚህ የዝናብ እጥረት ምክንያትት ረሀብ ይከሰታል የሚል ሥጋት እንደሌለው የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
«እርዳታ የሚሰጣቸውም ሆነ ለረሀብ የተጋለጡ ወገኖች የሉም» ሲሉ የግብርና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ብርሃኑ ለቪኦኤ ዘጋቢ እስክንድር ፍሬው ገልፀዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡