ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ለቦረና ዞን የድርቅ ተጎጂዎች እርዳታ በማድረስ ላይ እንደሚገኝ መንግሥት አስታወቀ። አስቸኳይ እርዳታ እንዲያገኙ በዞኑ አስተዳደር ለተለዩ ወደ 100 ሺሕ ለሚጠጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሰብል አርዳታ መላኩን የኦሮምያ ክልል አደጋ ሥጋት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ገረሙ ኦሊቃ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ግለሰቦችም በዞኑ በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ አሰባስበዋል።